American Medical Center Doctors
Dr. Akeza Teame earned an Associate Degree of Arts from Hesston College, a BS in genetics from the University of Kansas and his Doctor of Medicine (MD) from the University of Kansas School Of Medicine. He completed his residency in Internal Medicine and a Fellowship in Infectious Diseases (ID) at the Albert Einstein College of Medicine in New York City. Dr. Akeza is board-certified in Internal Medicine and Infectious Diseases (ID) in the US and licensed to practice medicine in several states in the US. He is also one of the six panel physicians in Ethiopia chosen by the CDC and the American Embassy to conduct medical evaluation for the US Embassy visa applicants. Dr. Akeza is the co-founder and Medical Director of American Medical Center and Saint Yared Hospital Holdings, P.L.C.
ዶ/ር አከዛ ጣእመ የባችለር ዲግሪያቸውን በጄኔቲክስ በአሜሪካ ከሚገኘው ሄስተን ኮሌጅ እና ካንሳስ ዩኒቨርሲቲ ካገኙ በኋላ የህክምና ትምህርታቸውን በካንሳስ ዩኒቨርሲቲ አጠናቀዋል፡፡ በመቀጠልም በውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻላይዜሽን እና በተላላፊ በሽታዎች ህክምና ሰብ-ስፔሻላይዜሽን በኒው ዮርክ ከሚገኘው አልበርት አይንስታይን ኮሌጅ አግኝተዋል፡፡ ዶ/ር አከዛ በውስጥ ደዌ እና በተላላፊ በሽታዎች ህክምና በአሜሪካ ቦርድ-ሰርቲፋይድ ናቸው፡፡ በአሜሪካ የበሽታ መከላከያ እና ቁጥጥር (CDC) እና በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የጉዞ ህክምና የማድረግ ፍቃድ ካላቸው 6 ሀኪሞች አንዱ ናቸው፡፡ ዶ/ር አከዛ የአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር እና የአቢሲንያ ሜዲካል ሴንተር መስራች እና ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ ከሳማሪታን የቀዶ ህክምና ማእከል እና የቅዱስ ያሬድ ሆስፒታል መስራቾችም አንዱ ናቸው፡፡
Dr. Tinsae Alemayehu earned his Doctorate Degree in Medicine and specialty training in Pediatrics and Child health from Addis Ababa University, College of Health Sciences. He has served at the medical schools of Tikur Anbessa (Addis Ababa University) and St. Paul’s teaching hospitals. He received his sub-specialty training in Pediatric infectious diseases from Addis Ababa University and McGill University, Canada. Dr. Tinsae is a full-time pediatrician/pediatric infectious diseases’ specialist and Medical Director at AMC. He is also one of the six panel physicians in Ethiopia chosen by the CDC and the American Embassy to conduct medical evaluation for the US Embassy visa applicants.
ዶ/ር ትንሳኤ አለማየሁ የህክምና የመጀመርያ ዲግሪያቸውን የህፃናት ህክምና ስፔሻላይዜሽን ስልጠናቸውን በአ.አ.ዩ. ጥቁር አንበሳ የህክምና ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡ በጥቁር አንበሳ እና በቅዱስ ጳውሎስ የህክምና ት/ቤቶች በማስተማር ያገለገሉ ሲሆን ከአ.አ.ዩ. እና በካናዳ ከሚገኘው የማጊል ዩኒቨርሲቲ የህፃናት ተላላፊ በሽታዎች ህክምና ሰብ-ስፔሻላይዜሽናቸውን አግኝተዋል፡፡ ዶ/ር ትንሳኤ በአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት፣ የህፃናት ተላላፊ በሽታዎች ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት እና ሜዲካል ዳይሬክተር ሆነው ያገለግላሉ፡፡ በአሜሪካ የበሽታ መከላከያ እና ቁጥጥር (CDC) እና በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የጉዞ ህክምና የማድረግ ፍቃድ ካላቸው 6 ሀኪሞች አንዱ ናቸው፡፡
Dr Nebiyu Asnake earned his doctor of medicine degree and from specialty certificate in Internal medicine from the Addis Ababa University medical school. He is an experienced physician who has worked at various reputable healthcare facilities. He completed his sub-specialty training in Gastroenterology and Hepatology at Ludwig Maximilian University in Germany and Apollo Teaching Hospitals in Hyderabad and Chennai, India. Dr Nebiyu is currently the deputy medical director of AMC and also works as a full-time Internist and Gastroenterologist/Hepatologist.
ዶ/ር ነብዩ አስናቀ የህክምና የመጀመርያ ዲግሪያቸውን እና የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻላይዜሽን ስልጠናቸውን ከ አ.አ.ዩ. ጥቁር አንበሳ የህክምና ት/ቤት ያጠናቀቁ ሲሆን በተለያዩ የህክምና ተቋማት የረዥም አመት የስራ ልምድ አካብተዋል፡፡ በተጨማሪም በጀርመን ከሚገኘው የሉድዊግ ማክሲሚላን ዪኒቨርሲቲ እና በህንድ ከሚገኘው አፖሎ ሆስፒታል የአንጀት እና ጉበት ህክምና ሰብ-ስፔሻላይዝ አድርገዋል፡፡ ዶ/ር ነብዩ ባሁኑ ሰአት የአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር ምክትል ሜዲካል ዳይሬክተር እና የውስጥ ደዌ/የአንጀት እና ጉበት ህክምና ስፔሻሊስት ሆነው ያገለግላሉ፡፡
Dr. Kale-Ab Tesfaye earned his Doctor of medicine degree from Jimma Institute of Health Sciences and received his Specialty Diploma in Pediatrics and Child Health from Addis Ababa University. He has worked at various reputable healthcare facilities since then and has served as an Honorary teaching staff at St. Paul’s Millennium Medical College. Dr Kale-Ab has worked as a Consultant Pediatrician at the United Nations Health Care Center (Addis Ababa) for two and half years before joining AMC as a full-time Pediatrician.
ዶ/ር ቃለአብ ተስፋዬ የህክምና የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከጅማ ዩኒቨርስቲ የህክምና ኢንስቲትዩት ያገኙ ሲሆን የህፃናት ህክምና ስፔሻላይዜሽን ስልጠናቸውን ከአ.አ.ዩ. ጥቁር አንበሳ የህክምና ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡ በተለያዩ የህክምና ተቋማት ከመስራት በተጨማሪ በቅዱስ ጳውሎስ የህክምና ት/ቤት በማስተማር አገልግለዋል፡፡ ዶ/ር ቃለአብ ለሁለት አመት ተኩል በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት የህክምና ማእከል ከሰሩ በኋላ ባሁኑ ሰአት በአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ሆነው ያገለግላሉ፡፡
Dr. Amanuel Abera earned his Doctorate Degree in Medicine from the University of Gondar College of Medicine and Health Sciences. He then received his specialty training in Internal Medicine from Addis Ababa University, College of Health Sciences and also earned his Masters’ Degree in International Health from the Institute of Tropical Medicine, Antwerp, Belgium. Dr. Amanuel is a full-time Internist at AMC.
ዶ/ር አማኑኤል አበራ የህክምና የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በጎንደር ሆስፒታል የህክምና ኮሌጅ በመቀጠልም የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻላይዜሽን ስልጠናቸውን በአ.አ.ዩ. ጥቁር አንበሳ የህክምና ት/ቤት ያጠናቀቁ ሲሆን በአለም አቀፍ ጤና አጠባበቅ የማስተርስ ዲግሪያቸውን በቤልጅየም ከሚገኘው የትሮፒካል ህክምና ኢንስቲትዩት አጠናቀዋል፡፡ ዶ/ር አማኑኤል ባሁኑ ሰአት በአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሆነው ያገለግላሉ፡፡
Dr Selamawit Tariku earned her doctor of medicine degree from Mekelle University and received her Specialty Diploma in Radiology from Addis Ababa University. She has previous experiences serving in Radiology units in public and private hospitals. Dr Selamawit is a full time Radiologist at AMC. She is also one of the six panel physicians in Ethiopia chosen by the CDC and the American Embassy to conduct medical evaluation for the US Embassy visa applicants.
ዶ/ር ሰላማዊት ታሪኩ የህክምና የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠልም የራድዮሎጂ ስፔሻላይዜሽን ስልጠናቸውን በአ.አ.ዩ. ጥቁር አንበሳ የህክምና ት/ቤት አጠናቀው በተለያዩ የህክምና ተቋማት አገልግለዋል፡፡ ዶ/ር ሰላማዊት ባሁኑ ሰአት በአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር በራድዮሎጂ ስፔሻሊስትነት ያገለግላሉ፡፡ በአሜሪካ የበሽታ መከላከያ እና ቁጥጥር (CDC) እና በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የጉዞ ህክምና የማድረግ ፍቃድ ካላቸው 6 ሀኪሞች አንዱ ናቸው፡፡
Dr. Demeke Mekonnen earned his degree of medicine from the College of Health Sciences, Jimma University in 2009. He completed his residency in Pediatrics and child health at the College of Health Sciences, Jimma University in 2013. He then completed his fellowship in Pediatric Cardiology at Wolfson medical center, Israel in 2017. He has also received training in medical education and curriculum development at Cardiff University in 2014. Dr Demeke is a part-time pediatric cardiologist at AMC.
ዶ/ር ደመቀ መኮንን የህክምና የመጀመርያ ዲግሪያቸውን እና የህፃናት ህክምና ስፔሻላይዜሽን ስልጠናቸውን በጅማ ዩኒቨርስቲ የህክምና ኢንስቲትዩት ያጠናቀቁ ሲሆን በመቀጠልም የህፃናት የልብ ህክምና ሰብ-ስፔሻላይዜሽናቸውን በዎልፍሰን ህክምና ማእከል (እስራኤል) አጠናቀዋል፡፡ በህክምና ትምህርት ቀረፃም በካርዲፍ ዩኒቨርሲቲ ሰልጥነዋል፡፡ ዶ/ር ደመቀ በአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር የህፃናት የልብ ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት ሆነው ያገለግላሉ፡፡
Dr. Selam Aberra, earned her doctor of medicine, (MD) from the University of Gondar and Health Sciences and completed her residency in psychiatry at Addis Ababa University, College of Medicine. She is a part-time Psychiatrist at AMC and assists the US embassy in screening and treating travelers with mental illness and substance-related problems.
ዶ/ር ሰላም አበራ የህክምና የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በጎንደር ሆስፒታል የህክምና ኮሌጅ በመቀጠልም የአእምሮ ህክምና ስፔሻላይዜሽን ስልጠናቸውን በአ.አ.ዩ. ጥቁር አንበሳ የህክምና ት/ቤት አጠናቀው በተለያዩ የህክምና ተቋማት አገልግለዋል፡፡ ዶ/ር ሰላም ባሁኑ ሰአት በአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር በአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት ሆነው ያገለግላሉ፡፡ በአሜሪካ ኤምባሲም የአእምሮ ህክምና እና የሱስ ህክምና ይሰጣሉ፡፡
Dr. Solomon G/Mariam earned his degree of medicine from the Aristotle University of Thessaloniki-Greece. He completed his residency in internal medicine at General Hospital of Athens, Greece. He completed his fellowship in cardiology at Janeio Hospital, Greece followed by a further 2 year fellowship in interventional Cardiology. Dr. Solomon is a member of the Greece Cardiologist Association and European Cardiology Association. Dr. Solomon is board certified to practice medicine in European Union countries. Dr. Solomon is a scientific associate of Janeio Hospital's Cardiologic Department in Greece. Dr. Solomon is a part-time adult cardiologist at AMC.
ዶ/ር ሰለሞን ገብረማርያም የህክምና የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በግሪክ ከሚገኘው ከአሪስቶትል ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ሲሆን የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻላይዜሽን ስልጠናቸውን ከአቴንስ ጄነራል ሆስፒታል (ግሪክ) በመቀጠልም የልብ ህክምና ሰብ-ስፔሻላይዜሽናቸውን በጃኔዮ ሆስፒታል (ግሪክ) አጠናቀዋል፡፡ በውስጥ ደዌ እና በልብ በሽታዎች ህክምና በአውሮፓ ህብረት ሀገሮች ሰርቲፋይድ ሲሆኑ በተለያዩ የህክምና ተቋማት የረዥም አመት የስራ ልምድ አካብተዋል፡፡ ዶ/ር ሰለሞን የግሪክ እና የአውሮፓ የልብ ህክምና ማህበር አባል ሲሆኑ ባሁኑ ሰአት የአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር በልብ በሽታዎች ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት ሆነው ያገለግላሉ፡፡
Dr. Dawit Solomon earned his Degree in doctor of medicine (MD) from Jimma University, College of Medicine and Health Sciences. He started his residency in Pathology at Suez Canal University, in Egypt and completed it at the Addis Ababa University College of Medicine. Dr. Dawit has undergone several in-depth short and intermediate-term fellowship attachments on renal pathology at different medical schools in the US, including the Mayo Clinic, in Rochester, Minnesota. He is the only pathologist responsible for dealing with renal biopsy at St. Paul Hospital Millennium Medical College and a part-time Pathologist at AMC.
ዶ/ር ዳዊት ሰለሞን የህክምና የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በጅማ ዩኒቨርስቲ የህክምና ኢንስቲትዩት ያጠናቀቁ ሲሆን በስነ-ደዌ (ፓቶሎጂ) ስፔሻላይዜሽናቸውን በስዊዝ ካናል ዩኒቨርሲቲ (ግብጽ) እና በአ.አ.ዩ. ጥቁር አንበሳ የህክምና ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡ ሜዮ ክሊኒክን ጨምሮ በኩላሊት ህክምና ፓቶሎጂ የተለያዩ ስልጠናዎችን በአሜሪካ ተከታትለዋል፡፡ ዶ/ር ዳዊት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እና የህክምና ት/ቤት የኩላሊት ህክምና ፓቶሎጂስት ሲሆኑ በአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር ፓቶሎጂስት ሆነው ያገለግላሉ፡፡
Dr. Zelealem Debebe earned her medical degree from Jimma University and her Bachelor of Science from King’s College in London, UK. Dr. Zelealem works as a nutritionist and dietician at AMC.
ዶ/ር ዘላለም ደበበ የህክምና የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በጅማ ዩኒቨርስቲ የህክምና ኢንስቲትዩት ያጠናቀቁ ሲሆን በለንደን፣ እንግሊዝ ከሚገኘው ከኪንግስ ኮሌጅ የባችለር ዲግሪያቸው አግኝተዋል፡፡ ዶ/ር ዘላለም በአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር የስነ-ምግብ ስፔሻሊስት ሆነው ያገለግላሉ፡፡
Dr. Maeida Oumer earned her Doctor of medicine (MD) from Gondar College of Health Science and Medicine. She is currently pursuing her training in a Master’s in Public Health program. She is one of the six-panel physicians in Ethiopia chosen by the CDC and the American Embassy to conduct medical evaluation for US Embassy visa applicants. Dr Maeida is currently serving as a general practitioner at AMC.
ዶ/ር ማይዳ ኡመር የህክምና ዲግሪያቸውን ከጎንደር ሆስፒታል የህክምና ኮሌጅ ያገኙ ሲሆን በተለያዩ የህክምና ተቋማት አገልግለዋል፡፡ ባሁኑ ሰኣትም በህብረተሰብ ጤና ዘርፍ የማስተርስ ዲግሪ ጥናታቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በአሜሪካ የበሽታ መከላከያ እና ቁጥጥር (CDC) እና በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የጉዞ ህክምና የማድረግ ፍቃድ ካላቸው 6 ሀኪሞች አንዱ ናቸው፡፡ ዶ/ር ማይዳ በአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር በጠቅላላ ሀኪምነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
Dr Kalkidan Alachew earned her Doctor of medicine (MD) from Gondar College of Health Sciences and completed her specialty training in Internal medicine at the Addis Ababa University medical school. She has served at various reputable healthcare facilities. She completed her sub-specialty training in Endocrinology at the Addis Ababa University medical school. Dr Kalkidan is currently serving as an Endocrinologist at AMC.
ዶ/ር ቃልኪዳን አላቸው የህክምና የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከጎንደር ሆስፒታል የህክምና ኮሌጅ ያገኙ ሲሆን እና የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻላይዜሽን ስልጠናቸውን ከ አ.አ.ዩ. ጥቁር አንበሳ የህክምና ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡ በተለያዩ የህክምና ተቋማት ያገለገሉ ሲሆን በ አ.አ.ዩ. ጥቁር አንበሳ የህክምና ት/ቤት በኤንዶክሪኖሎጂ (የስኳር እና የሆርሞን ህክምና) ሰብ-ስፔሻላይዝ አድርገዋል፡፡ ዶ/ር ቃልኪዳን በአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር ኤንዶክሪኖሎጂስት (የስኳር እና የሆርሞን ህክምና ስፔሻሊስት) ሆነው ያገለግላሉ፡፡
Dr Rahel Gashu earned her Doctor of medicine (MD) from Mekelle University. She is currently pursuing her training in a Master’s in Public Health program. Dr Rahel is currently serving as a general practitioner at AMC and educational and training specialist at Caduceus pharmaceuticals PLC.
ዶ/ር ራሄል ጋሹ የህክምና ዲግሪያቸውን ከመቀሌ ሆስፒታል የህክምና ኮሌጅ ያገኙ ሲሆን ባሁኑ ሰኣት በህብረተሰብ ጤና ዘርፍ የማስተርስ ዲግሪ ጥናታቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ዶ/ር ራሄል በአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር በጠቅላላ ሀኪምነት እና በካዱስየስ ፋርማሲውቲካልስ የህክምና ስልጠና ስፔሻሊትነት ያገለግላሉ፡፡
Dr Emnet Belete earned her Doctor of medicine (MD) from Bethel medical college. She is currently serving as a general practitioner and coordinator of the COVID19 treatment unit at AMC.
ዶ/ር እምነት በለጠ የህክምና ዲግሪያቸውን ከቤተል ሆስፒታል የህክምና ኮሌጅ ያገኙ ሲሆን ባሁኑ ሰኣት በአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር በጠቅላላ ሀኪምነት እና የኮቪድ ህክምና ማእከል አስተባባሪነት ያገለግላሉ፡፡
Dr Segen Zerabruk earned her Doctor of medicine (MD) from Mekelle University. She is currently serving as a general practitioner at AMC.
ዶ/ር ሰገን ዘርአብሩከ የህክምና ዲግሪያቸውን ከመቀሌ ሆስፒታል የህክምና ኮሌጅ ያገኙ ሲሆን ባሁኑ ሰኣት በአሜሪካን ሜዲካል ሴንተር በጠቅላላ ሀኪምነት ያገለግላሉ፡፡